በለውጡ የተመዘገቡ ስኬቶችን ለማስቀጠል በቁርጠኝነት መረባረብ ይገባል – አቶ ሙስጠፌ መሃመድ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በለውጡ በተለያዩ ዘርፎች የተመዘገቡ ስኬቶችን አጠናክሮ ለማስቀጠል ሁሉም በቁርጠኝነት ሊረባረብ ይገባል ሲሉ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሃመድ ገለጹ፡፡
“ትናንት ፣ ዛሬና ነገ ለኢትዮጲያ ልዕልና “በሚል መሪ ሃሳብ በመጋቢት 24 ሀገራዊ ለውጥ የተገኙ ስኬቶችና ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት በጅግጅጋ ተካሂዷል።
አቶ ሙስጠፌ በመድረኩ ባስተላለፉት መልዕክት፥ ሀገራዊ ለውጡ በኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ማህበራዊ መስኮች አመርቂ ስኬት ማስገኘቱን ተናግረዋል፡፡
በለውጡ በየዘርፉ የተመዘገቡ ስኬቶችን ለማስቀጠልም ሁሉም በቁርጠኝነት ሊረባረብ እንደሚገባ ነው ያሳሰቡት፡፡
በመድረኩ ላይ ከለውጡ ወዲህ በሀገሪቱና በክልሉ በተለያዩ መስኮች የተገኙ ውጤቶችና ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ ጽሑፍ ቀርቦ ውይይት ተደርጓል።
በመድረኩ የተሳተፉ የክልሉ የሃገር ሽማግሌዎች÷ በሶማሌ ክልል ከለውጡ ወዲህ በርካታ የልማትና የሰላም ሥራዎች እንደተከናወኑ መግለጻቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡