አቶ አረጋ ከበደ እና ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) በባሕር ዳር ከተማ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስን (ዶ/ር) ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች እና አምባሳደሮች በባሕር ዳር ከተማ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ፡፡
በጉብኝታቸውም፤ የኮሪደር ልማቱን ተከትሎ በጣና ሐይቅ ዙሪያ የሚሠሩ የቱሪስት መዳረሻዎችን ተመልክተዋል።
በተጨማሪም የባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ግንባታ እና የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሕንጻ የእድሳት ሥራዎችን መመልከታቸውን የክልሉ ርዕሰ መሥተዳድር ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡
ባሕር ዳር ሰላሟን አስጠብቃ በልማት ላይ የምትገኝ ውብ ከተማ መሆኗን በዚሁ ወቅት ጎብኝዎቹ ገልጸዋል፡፡
የሀገር ውስጥ እና የውጭ ጎብኝዎችን ቀልብ የምትስብ፣ ጣና ፎረምን የመሳሰሉ ታላላቅ ሁነቶችንም የምታስተናግድ ከተማ መሆኗንም ተናግረዋል።