Fana: At a Speed of Life!

ሚኒስቴሮቹ እና ተጠሪ ተቋሞቻቸው የለውጡን ዓመታት የተመለከቱ ውይይቶች አካሄዱ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ቱሪዝም ሚኒስቴር እና ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ከተጠሪ ተቋሞቻቸው ጋር በመሆን ያለፉትን ሰባት የለውጥ ዓመታት የተመለከቱ የፓናል ውይይቶችን አካሄዱ፡፡

የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ ተቋማቸው ከተጠሪ ተቋማቱ ጋር ባካሄደው የፓናል ውይይት ላይ እንዳሉት፤ የለውጡ ዓመታት በፅንፎች ተወጥሮ የነበረ የፖለቲካ ዕይታችን እንዲለወጥ እና በብዝኃ ኢኮኖሚ ዘርፎች በተለይም ሀገራችንን ከተረጂነት ለማላቀቅ መሰረት የተጣለበት ነው፡፡

በቀደሙ ዓመታት ሳናያቸው ተሸፍነው የነበሩ ሀብቶቻችንን ያየንበትና መጠቀም የቻልንበት ጊዜ ነበር ማለታቸውን የቅርስ ባለስልጣን መረጃ አመላክቷል፡፡

በቀጣይም በተሰማራንበት የሥራ መስክ ውጤት በማስመዝገብ ለመጪው ትውልድ የምናስረክበው ስራ እንሥራ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በተመሳሳይ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ መሥሪያ ቤታቸው ከተጠሪ ተቋማቱ ጋር ባካሄደው የፓናል ውይይት ላይ ባደረጉት ንግግር፤ ለውጡ ያልነካካው ዘርፍ የለም፤ በጋራ በመናበብ መሥራት ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡

ሁላችንም ዘመኑን በዋጀ ለውጥና አሠራር ራሳችንን እያበቃን መሥራት አለብን ሲሉ መልዕክት ማስተላለፋቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.