Fana: At a Speed of Life!

ብልጽግና ፓርቲ ከተረጂነት እና ከልመና መውጣት አለብን ብሎ ያምናል – አቶ አደም ፋራህ

 

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ ኅብረ-ብሔራዊነት የተላበሰች ሀገር በመሆኗ ጠንካራ ሀገረ መንግሥት ለመመስረት ሁሉንም ማቀፍ እንደሚገባ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ እና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ ገለፁ።

ብልፅግና ፓርቲ የኢኮኖሚ ነፃነት የኑሮ ውድነት ችግር በዘላቂነት ለመፍታት ያግዛል ብሎ እንደሚያምን አቶ አደም አስረድተዋል፡፡

በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ነፃነት ለማረጋገጥ ምርት እና ምርታማነትን ለማሳደግ በሁሉም ዘርፎች ያሉ እድሎችን በአግባቡ መጠቀም ላይ በትኩረት መሰራቱን አንስተዋል፡፡

ፓርቲው ባለፉት ሰባት የለውጥ ዓመታት በኢትዮጵያ ሁለንተናዊ እድገት ለማረጋገጥ የያዛቸውን ሐሳቦች ተግባራዊ ለማድረግ እና የተሰጠውን ታሪካዊ አደራ ለመወጣት ርብርብ እያደረገ መሆኑንም አንስተዋል፡፡

ለአብነትም ባለፉት ዓመታት በግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ ቱሪዝም፣ ማዕድን እንዲሁም በሁሉም ዘርፎች ምርት እና ምርታማነት ከማሳደግ አንፃር በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን አብራርተዋል፡፡

ተረጂዎችን ወደ ምርታማነት ለማሸጋገር የተቀናጀ እንቅስቃሴ መጀመሩንም አስታውቀዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.