Fana: At a Speed of Life!

ፋሲል ከነማ ወልዋሎ ዓዲ-ግራት ዩኒቨርሲቲን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ23ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሃ ግብር ፋሲል ከነማ ወልዋሎ ዓዲ-ግራት ዩኒቨርሲቲን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸነፈ፡፡

የፋሲል ከነማን የማሸነፊያ ግቦች ጌታነህ ከበደ እና ሸምሰዲን መሐመድ ከመረብ አሳርፈዋል፡፡

ወልዋሎ ዓዲ-ግራት ዩኒቨርሲቲን ከሽንፈት ያልታደገችውን ብቸኛ ግብ ቡልቻ ሹራ አስቆጥሯል፡፡

ፋሲል ከነማ ማሸነፉን ተከትሎ ወደ 7ኛ ደረጃ ከፍ ሲል፥ ወልዋሎ ዓዲ-ግራት ዩኒቨርሲቲ በደረጃ ሰንጠረዡ ግርጌ ለመቆየት ተገዷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.