በጋምቤላ ክልል ከ28 ሺህ በላይ ተማሪዎች የምገባ አገልግሎት ተጠቃሚ ሆኑ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በጋምቤላ ክልል ከ28 ሺህ በላይ ተማሪዎች የትምህር ቤት ምገባ መርሐ ግብር ተጠቃሚ መሆናቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል፡፡
በቢሮው የተማሪዎች ምገባና ሥርዓተ ምግብ አስተባባሪ አቶ ጃሙስ ጆኝ እንዳሉት÷በ2017 ዓ.ም እየተተገበረ ባለው የተማሪዎች ምገባ መርሐ ግብር በምግብ ችግር ሳቢያ ከት/ቤት የሚቀሩ ተማሪዎችን ቁጥር ቀንሷል፡፡
በአሁኑ ወቅትም በ8 ወረዳዎች በሚገኙ 56 ትምህርት ቤቶች የምግበ አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡
ከእነዚህ መካከልም 35 ት/ቤቶች በክልሉ መንግስት ወጪያቸው የሚሸፈን ሲሆን÷ቀሪዎቹ ደግሞ ከወረዳና ከማህበረሰብ ተሳትፎ በሚገኝ ድጋፍ የሚሸፈን መሆኑን ጠቅሰዋል።
የምገባ መርሐ ግብሩ ተማሪዎች በትምህርታቸው መሠረታዊ ለውጥ እንዲያመጡ እንደሚያግዝ መጠቆሙን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
በክልሉ የተጀመረው የተማሪዎች ምገባ ፕሮግራም ዘለቂነት እንዲኖረው የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን እንዲወጡም ጥሪ ቀርቧል፡፡