Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ መድን ሀዋሳ ከተማን በማሸነፍ መሪነቱን አጠናከረ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ23ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ኢትዮጵያ መድን ሀዋሳ ከተማን 2 ለ 1 በማሸነፍ መሪነቱን ማጠናከር ችሏል፡፡

ምሽት 12 ሰዓት በተደረገው ጨዋታ የኢትዮጵያ መድንን የማሸነፊያ ግቦች መሐመድ አበራና አቡበከር ሳኒ ሲያስቆጥሩ ÷የሀዋሳ ከተማን ብቸኛ ግብ ደግሞ ቸርነት አውሽ ከመረብ አሳርፏል፡፡

ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ መድን በ44 ነጥብ መሪነቱን ሲያጠናክር፥ ሀዋሳ ከተማ ደግሞ በ20 ነጥብ 15 ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡

ቀደም ሲል ቀን 9 ሰዓት ላይ በተካሄደ ጨዋታ ወላይታ ድቻ ፍፁም ግርማ ባስቆጠራት ግብ መቐለ 70 እንደርታን 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡

ወላይታ ድቻ ማሸነፉን ተከትሎ በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ 36 ነጥብ በመያዝ 2ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ፥ መቐለ 70 እንደርታ ደግሞ በ25 ነጥብ 14 ላይ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.