Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ከባቢን ለመፍጠር ቁርጠኛ መሆኗን ገለጸች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ከባቢን ለመፍጠር ቁርጠኛ መሆኗን የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ለሊሴ ነሜ (ኢ/ር) ገለጹ፡፡

ለሊሴ ነሜ (ኢ/ር) እና ሌሎች አመራሮች በብራዚል በተካሄደው 11ኛው የብሪክስ የአካባቢ ጥበቃ ስብሰባ ላይ ተሳትፈዋል፡፡

ዋና ዳይሬክተሯ በስብሰባው ባደረጉት ንግግር÷ ኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ከባቢን ለመፍጠር፣ ለዘላቂ ልማትና ለአካባቢ ጥበቃ ቁርጠኛ መሆኗን ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መሪነት እየተገበረች የምትገኘውን የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ለአብነት አንስተዋል፡፡

ዓለም አቀፍ ግቦችን ለማሳካት እንዲቻል የብሪክስ አባል ሀገራት በእውቀት፣ በቴክኖሎጂ ሽግግርና በፋይናንስ ጉዳዮች ትብብራቸውን ሊያጠናከሩ እንደሚገባ ማስገንዘባቸውንም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.