Fana: At a Speed of Life!

የሹዋሊድ በዓል ከነገ ጀምሮ በድምቀት ይከበራል

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሐረሪ ክልል ከነገ ጀምሮ የሚከበረው የሹዋሊድ በዓል በስኬት ለማጠናቀቅ የሚያስችል ዝግጅት መጠናቀቁን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ረምዚ ሱልጣን፤ በዓሉ በድምቀት ተከብሮ እንዲጠናቀቅ ከሁሉም ወረዳዎች ከተውጣጡ የጸጥታ አካላት ጋር የጋራ ምክክር በማድረግ ወደ ሥራ መገባቱን አረጋግጠዋል፡፡

በበዓሉ ዋዜማና በዕለቱ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይኖር ከታች የተዘረዘሩት አካባቢዎች መንገዶች ለትራፊክ ዝግ ይሆናሉ ብለዋል፡፡

በዚሁም መሠረት፡-

  • ነገ ከጠዋቱ 12 ሠዓት ጀምሮ በራስ ሆቴል ወደ ርዕሰ መሥተዳድር ጽሕፈት ቤት፣ በሥላሴ ወደ ትራፊክ መብራት የሚወስደው መንገድ፣
  • እንዲሁም ከምሽቱ 12 ሠዓት ጀምሮ በጎዳና ካፌ፣ በሸንኮር፣ በሸዋበር ወደ ቀድሞ ርዕሰ መሥተዳድር ጽሕፈት ቤት እና ወደ ፈረስ መጋላ፤
  • በዱክበር፣ በፈላና በር፣ በኤረር በር፣ በሰንጋ በር ወደ ፈረስ መጋላ ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆን ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም በዋዜማው ከምሽት ጀምሮ ሥነ-ሥርዓቱ በሚከናወንበት እና ዝግ በሚሆኑ መንገዶች አካባቢ ለአጭርም ሆነ ለረጅም ሠዓት ተሽከርካሪ ማቆም የተከለከለ መሆኑን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.