ወደ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከ53 ሺህ ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ገብቷል
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ለ2017/18 የምርት ዘመን ከተመደበው ውስጥ እስከ አሁን ከ53 ሺህ ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ መረከቡን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ግብርና ቢሮ አስታውቋል።
ወደ ክልሉ የገባውን የአፈር ማዳበሪያም ከሥር ከሥር ወደ ቀበሌዎች የማሠራጨት ሥራ እየተከናወነ መሆኑን በቢሮው የግብዓት አቅርቦት እና ምርት ግብይት ዳይሬክተር ተስፋዬ በቀለ ተናግረዋል፡፡
እስከ አሁንም ከ5 ሺህ ኩንታል በላይ ማዳበሪያ ለአርሶ አደሩ መሰራጨቱን ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ገልጸዋል፡፡
በምርት ዘመኑ ለክልሉ ከተመደበው 231 ሺህ 340 ኩንታል ከ53 ሺህ ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ መረከባቸውን ጠቅሰው፤ ቀሪውን በፍጥነት ወደ ክልሉ ለማስገባት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እየተሠራ ነው ብለዋል፡፡
በሰለሞን ይታየው