Fana: At a Speed of Life!

የቤልጂየም እና ሉክሰምበርግ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የቤልጂየም እና ሉክሰምበርግ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ እንዲሳተፉ በቤልጂየም የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጥሪ አቀረበ፡፡

ኤምባሲው በኢትዮጵያ ያሉ የኢንቨስትመንት አማራጮችን የሚያስተዋውቅ የንግድ እና ኢንቨስትመንት ማስተዋወቂያ መድረክ አካሂዷል።

አምባሳደር እሸቴ ጥላሁን በዚሁ ወቅት በኢትዮጵያ የተካሄዱ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ምቹ የኢንቨስትመንት አማራጮች መፍጠራቸውን ጠቅሰው፤ የቤልጂየም እና ሉክሰምበርግ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

ግብርና፣ ፋርማሲ፣ ቱሪዝም፣ ማዕድን እና ቴክኖሎጂ የኢትዮጵያ መንግሥት ቀዳሚ ትኩረት የሰጣቸው የኢንቨስትመንት ዘርፎች ናቸው ማለታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡

በመድረኩ ለተሳተፉ ኩባንያዎች እና የንግድ ማኀበረሰቦች በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት አማራጮች ዙሪያ ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.