Fana: At a Speed of Life!

ፌዴራል ፖሊስ ለሕዳሴ ግድብ ከ254 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር በላይ ማዋጣቱ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ፌዴራል ፖሊስ ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቦንድ ግዥን ጨምሮ የተለያዩ የገቢ ማሰባሰቢያ በማካሄድ ከ254 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር በላይ በማዋጣት ገቢ ማድረጉን ገለጸ።
የፌዴራል ፖሊስ ቃል-አቀባይ ረዳት ኮሚሽነር ሞገስ ቸኮል የተቋሙ አመራርና አባላት የታላቁን ሕዳሴ ግድብ ሁለንተናዊ ደኅንነት ከመጠበቅ ባሻገር የዜግነት ኃላፊነትቱን ለመወጣት የተለያዩ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራሞች ማካሄዱን አንስተዋል።
ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በዘመናዊ ጀልባ የታገዘ የተጠናከረ ጥበቃ ለማድረግ ፖስታል ጋርድ ፖሊስ አደራጅቶ ወደ ተግባር ለመግባት ዝግጅት ማጠናቀቁን መግለፃቸውን የፌዴራል ፖሊስ መረጃ አመላክቷል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.