Fana: At a Speed of Life!

የግብርና ምርቶችን ለማቀነባበር ወደ ፓርኩ የሚገቡ ባለሃብቶች ቁጥር ጨምሯል ተባለ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የግብርና ምርቶችን ለማቀነባበር ወደ ይርጋለም የተቀናጀ የግብርና ምርቶች ኢንዱስትሪ ፓርክ የሚገቡ ባለሃብቶች ቁጥር መጨመሩ ተገለጸ፡፡

የሲዳማ ክልል ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኃይሉ የተራ፤ የአምራች ባለሃብቶቹ ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ በመጨመሩ ከ24 ሺህ ለሚበልጡ ዜጎች ቋሚ የሥራ ዕድል መፍጠር ተችሏል ብለዋል፡፡

በፓርኩ ሥራ ለመጀመር ውል የገቡ 32 ፕሮጀክቶች፤ ሼድ በመገንባት፣ ብድር በማጽደቅና በሌሎች ሂደቶች ላይ መሆናቸውንም ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡

ከእነዚህ መካከልም አብዛኞቹ ቡና ወደ ማቀነባበር የሚገቡ መሆናቸውን ጠቁመው፤ ስምንት ፋብሪካዎች ደግሞ የአቮካዶ ዘይት፣ ማር፣ ቡና፣ ወተትና ጁስ በማቀነባበር ወደ ምርት መግባታቸውን አብራርተዋል፡፡

በተጨማሪም ስምንት የሀገር ውስጥና የውጭ ባለሀብቶች የግብርና ምርቶችን ለማቀነባበር በአዲስ መልክ ውል መፈጸማቸውን አስታውቀዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.