Fana: At a Speed of Life!

መጋቢት 24 የለውጥ ጮራና የብልፅግና ዘመን ጅማሮ ነው – አቶ አረጋ ከበደ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) መጋቢት 24 የለውጥ ጮራ መባቻና የብልፅግና ዘመን ጅማሮ ነው ሲሉ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ ገለፁ፡፡

አቶ አረጋ ከበደ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መረጃ÷ ሰባት የለውጥ ዓመታትን በድል ተሻግረን የሰነቅናቸውን ታላላቅ ሕልሞች እያሳካን፣ የገጠሙንን ፈተናዎች ከህዝባችን ጋር በቅንጅት በመስራት እየተሻገርን እንገኛለን ብለዋል፡፡

ለህዝባችን የሚበጁ አያሌ ተግባራትን እያከናወንን እንገኛለን ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ÷ መጋቢት 24 የትልሞቻችን ሁሉ የስኬት ጫፍ መጀመሪያ፣ የለውጥ ጮራ መባቻና የብልፅግና ዘመን ጅማሮ ነው ሲሉም ገልጸዋል።

በብልፅግና ዘመን ስብራቶችን የሚጠግኑ፣ የምናብን ከፍታና የተስፋዎችን ጥልቀት የሚመጥኑ የለውጥ ስራዎች ጥልቀትና ጥራት ባለው መልኩ በከተማና በገጠር እየተከናወኑ እንደሚገኙም አመላክተዋል፡፡

መዳረሻዎቻችን ከመንገዶቻችን ጋር የተሰናሰሉ፣ የህዝባችንን ዘላቂ ተጠቃሚነት መረጋገጣቸውን የሚመሰክሩ የለውጥ አሻራዎች ህያው ማሳያ ከተሞቻችን መካከል ደግሞ አንዷ የደሴ ከተማ ናት ሲሉም አክለዋል፡፡

በደሴ ከተማ ከቧንቧ ውሃ አደባባይ እስከ ወሎ ባህል አምባ የሚደርስ 1 ነጥብ 89 ኪሎ ሜትር የሚሸፍንና 46 ነጥብ 5 ሜትር ስፋት ያለው የኮሪደር ልማት፣ ቅልጥፍናና ጥራትን የሚጨምር የስማርት ሲቲ ፕሮጀክት እየተሰራ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.