Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 122 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር ለደንበኞቹ ደለደለ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሀገሪቱን የገቢ ንግድ ለማሳለጥ ከፍተኛ የሆነ የውጭ ምንዛሪ ለደንበኞቹ እያቀረበ እንደሚገኝ ገለፀ፡፡

በዚህም መሰረት በአጠቃላይ 711 የባንኩ ደንበኞች ያቀረቡትን ጥያቄዎች በመገምገም ከቀረቡት ጥያቄዎች ውስጥ 98 በመቶ የሚሆነውን መመለሱን አስታውቋል።

በዚህም ለደንበኞች በድምሩ የ122 ነጥብ 5 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ድልድል ማድረጉን ገልፆል፡፡

በተጨማሪም የቀሩት ጥቂት ደምበኞች ጥያቄ ተጨማሪ የመረጃ ማጣራት ስራ ተሰርቶ በቅርቡ የሚታይላቸው ይሆናል።

በቀጣይም ለደንበኞቹ የውጪ ምንዛሪ ጥያቄ፤ ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት ባንኩ ዝግጁ መሆኑንም ጠቁሟል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.