Fana: At a Speed of Life!

የአማራ ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍ የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት እየተካሄደ ነው

የአማራ ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአማራ ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍ የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት በባህር ዳር ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

የመክፈቻ ሥነ ሥርዓቱ የሀገራዊ ምክክር ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርአያ (ፕ/ር) እና ሌሎች ኮሚሽነሮች፣ የሃይማኖት አባቶችና የህብረተሰብ ተወካዮች በተገኙበት ነው እየተካሄደ የሚገኘው።

ኮሚሽነር መላኩ ወልደማርያም በዚሁ ወቅት፥ ሀገሪቱ በመጣችበት የጦርነት አዙሪት ህይወት ከመጥፋት፣ ከስደትና ከውድቀት ውጭ ያተረፈችው ነገር የለም ብለዋል።

ይህንን የጦርነት አዙሪት ለማስቆምና በመነጋገር አዲስ የፖለቲካ ሥርዓት ለማዋለድ ሀገራዊ ምክክር መጀመሩን ገልጸው፥ ግጭት በቃ ልንል ይገባል ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል።

በክልሉ የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ሚያዚያ 4 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚካሄድ ተገልጿል።

በዚህም አጠቃላይ 4 ሺህ 500 የማህበረሰብ ተወካዮች በመጀመሪያዎቹ 4 ቀናት እንደሚሳተፉ ይጠበቃል።

በቀጣይም የማህበረሰብ ተወካዮች፣ የመንግስት አካላት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች፣ የማህበራትና ተቋማት ተወካዮች ይወያያሉ ተብሏል።

በአጠቃላይ በክልሉ ከ6 ሺህ በላይ ተሳታፊዎች በአጀንዳ ማሰባሰብ ምዕራፉ እንደሚሳተፉ ኮሚሽኑ ገልጿል።

በመሣፍንት እያዩ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.