Fana: At a Speed of Life!

ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ለሹዋሊድ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ለሹዋሊድ ባህላዊ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ባስተላለፉት መልዕክት÷ ከለውጡ ማግስት ጀምሮ የሹዋሊድ በዓል የህዝብ ለህዝብ ትስስርን ለማጎልበት እና ህብረ ብሄራዊ አንድነትን ለማጠናከር በሚያስችል መልኩ እየተከበረ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

ሹዋሊድ የቱሪዝም ዘርፉን በማነቃቃት በኩል ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው እና በዩኔስኮ የዓለም ቅርስነት የተመዘገበ አንዱ የለውጡ ፍሬያችን ነው ሲሉም አመላክተዋል።

ሹዋሊድ የሀረሪ ህዝብ ባህላዊ በዓል ሲሆን÷ በ2016 ዓ.ም ኢትዮጵያ በዩኔስኮ የዓለም ቅርስነት ማስመዝገቧንም አስታውሰዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.