Fana: At a Speed of Life!

አትሌት ደሳለኝ ዳኘው እና የግሌ እሸቱ በ2017 የጅማ ታላቁ ሩጫ አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አትሌት ደሳለኝ ዳኘው እና አትሌት የግሌ እሸቱ በ2017 የጅማ ታላቁ ሩጫ ውድድር አሸነፉ።

ዛሬ ማለዳ በጅማ ከተማ በተደረገ የወንዶች 15 ኪሎ ሜትር ውድድር አትሌት ደሳለኝ ዳኘው በአንደኛነት ሲያጠናቅቅ፤ ጃፋር ጀማል ሁለተኛ እንዲሁም አብዮት ሞገስ ሦስተኛ በመሆን ውድድራቸውን ጨርሰዋል፡፡

በተመሳሳይ በሴቶች በተደረገ የ15 ኪሎ ሜትር ውድድር አትሌት የግሌ እሸቱ በቀዳሚነት ስታጠናቅቅ፤ ሃና ዓለማየሁ እና አና ላውልሄር ተከታትለው በመግባት ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃን ይዘዋል።

የቱሪዝም ሚኒስቴር ከታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ያካሄደው “ኢትዮጵያን ልወቅሽ” የሩጫ ውድድር በርካታ ስፖርተኞች ተሳትፈውበታል።

በውድድሩ የተገኙት በቱሪዝም ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ኮንቬንሽን ቢሮ ሥራ አስፈፃሚ ጌትነት ግዛው እንደገለፁት፤ ከዚህ ቀደም ቱሪዝም ከስፖርት ዘርፉ ጋር በማስተሳሰር መስራት አልተለመደም።

አሁን ግን ቱሪዝምን ከስፖርት ጋር አቀናጅቶ ለውጤት መስራት መጀመሩን አንስተው፤ ከታላቁ ሩጫ ጋር በመተባበር ውድድሮች እየተደረጉ መሆናቸውን ለአብነት አንስተዋል።

በዳዊት መሐሪ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.