በአማራ ክልል ትናንት የተጀመረው የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍ ዛሬም ቀጥሏል
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአማራ ክልል ያስጀመረው የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍ ዛሬም ቀጥሎ እየተካሄደ ነው።
በዚህም ከዛሬ ጀምሮ በሦስት ክላስተሮች ከ4 ሺህ 500 በላይ የሕብረተሰብ ክፍሎች ተወካዮች በቡድን ተከፋፍለው በአጀንዳዎቻቸው ላይ እየተወያዩ ነው።
ውይይቱ እየተካሄደ የሚገኘው በባሕርዳር ከተማ በሚገኘው በአማራ ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት ነው።
የሕብረተሰብ ተወካዮቹ ከነገ በስቲያ ለሀገራዊ ምክክር የሚወክሏቸውን ተሳታፊዎች በመምረጥ እና አጀንዳዎቻቸውንም ለኮሚሽኑ በማስረከብ የተያዘላቸውን መርሐ-ግብር ያጠናቅቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የሕብረተሰብ ተወካዮች ውይይት እንደተጠናቀቀም የባለድርሻ አካላት ውይይት ይቀጥላል ተብሏል፡፡
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከመጋቢት 27 እስከ ሚያዝያ 4 ቀን 2017 ዓ.ም በአማራ ክልል ከ6 ሺህ 500 በላይ ተወካዮች የሚሳተፉበት የአጀንዳ ምክክር እያካሄደ ይገኛል።
በመሳፍንት እያዩ