የትግራይ ክልል ተወላጆች ሕዝባዊ የምክክር መድረክ እያካሄዱ ነው
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የትግራይ ክልል ተወላጆች አስተባባሪ ኮሚቴ በአዲስ አበባ ከተማ ከሚኖሩ የክልሉ ተወላጆች ጋር በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ሕዝባዊ የምክክር መድረክ እያካሄደ ነው።
በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄደ የሚገኘውን የምክክር መድረክ የትግራይ ክልል ተወላጆች አስተባባሪ ኮሚቴ እንዳዘጋጀው ተገልጿል።
የክልሉ ሕዝብ የዴሞክራሲና የልማት ጥያቄዎች የሚፈቱበትን ሁኔታ እውን ለማድረግ ከየትኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ነፃ የሆነ የሲቪክ ማሕበረሰብ ድርጅት ማቋቋም እንደሚያስፈልግ በመድረኩ ተነስቷል፡፡
በተጨማሪም በክልሉ ያሉ የታጠቁ ኃይሎች ትጥቃቸውን ፈትተው ወደ መደበኛ ሕይዎታቸው እንዲመለሱ እና በክልሉ የሚታዩ ችግሮችን ለመፍታት የሁሉም አካላት ርብርብ ያስፈልጋል ነው የተባለው።
በየሻምበል ምኅረት