Fana: At a Speed of Life!

የሹዋሊድ በዓል ዓለም አቀፍ ቅርስነቱን በሚመጥን መልኩ በድምቀት ተከብሮ ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሹዋሊድ በዓል ዓለም አቀፍ ቅርስነቱን በሚመጥንና ኢትዮጵያዊ እሴቶችን ባንፀባረቀ መልኩ በድምቀት ተከብሮ መጠናቀቁን የሐረሪ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ኦርዲን በድሪ አስታወቁ፡፡

ርዕሰ መሥተዳድሩ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ የሹዋሊድ በዓል ባህላዊ ሥርዓቱንና እሴቱን በጠበቀ መልኩ በድምቀት ተከብሯል ብለዋል፡፡

በዓሉ በስኬት እንዲጠናቀቅ አስተዋጽኦ ላደረጉ የክልሉ ነዋሪዎች፣ ወጣቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሐይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ የፀጥታ አካላት፣ የአጎራባች ክልሎች ልዑካን እንዲሁም የሚዲያ አካላትን አመሥግነዋል፡፡

ሐረር የቱሪዝም ማዕከልነቷን የሚያሳድጉ እንዲሁም የከተማዋን ታሪክና ስም በሚመጥን መልኩ እየሠራናቸው ያሉ ሥራዎችን አጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉም አረጋግጠዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.