Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ገና አውቃ ያልጨረሰቻቸው የማዕድን ፀጋዎች አሏት – ሀብታሙ ተገኝ (ኢ/ር)

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በማዕድን ዘርፍ ያላትን ሀብት አውቃ እንዳልጨረች እና የማዕድን ሀብቷ ከፍተኛ እንደሆነ የማዕድን ሚኒስትር ሀብታሙ ተገኝ (ኢ/ር) ገለፁ፡፡

ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ የአፍሪካ ሀገራት በማዕድን ዘርፍ ያላቸውን ሀብት አውቀው እንዳልጨረሱ ጠቅሰው፤ በዘርፉ ብዙ ያልተሰሩ ብዙ ቀሪ ሥራዎች እንዳሉ ጠቁመዋል።

የማዕድን ሃብቱን ለመጠቀም እና ያለውን ሃብት ለይቶ ለማወቅ ብዙ መስራት ይጠበቃል ብለዋል፡፡

በተጨማሪም ምን ያህል የማዕድን ሀብት እንዳለ የት እንዳለ ለማወቅ ስንት ዓመት ሊወስድ ይችላል የሚለውን ማጣራት እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡

በሁሉም የማዕድን ዘርፎች ላይ ትኩረት ተሠጥቶ እየተሰራ መሆኑን ገልጸው፤ ዘርፉ ትልቅ ኢንቨስትመንት፣ ቴክኖሎጂ እና ጊዜ እንደሚፈልግም አብራርተዋል።

የተጠና ጥናት ካለ እና ሀብቱን የምናውቅ ከሆነ የማዕድን ሥራ ቀላል ነው ያሉት ሚኒስትሩ፤ የማዕድን ትልቁ ሥራ ፍለጋው እንጂ ማውጣቱ አይደለም ብለዋል።

አሁን በዘርፉ ጥሩ መሻሻሎች መኖቸራውን አንስተው፤ የማዕድን ልማት በመንግስት እና በግል ዘርፉ ትብብር እየተሰራበት እንደሆነ ጠቁመዋል።

የማዕድን ሀብትን ለይቶ ጥቅም ላይ ለማዋል በሚቀጥሉት አስር ዓመታት የሚሰሩ በርካታ ሥራዎች እንዳሉም ገልፀዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.