የጦላይ ከፍተኛ ባለሌላ ማዕረግተኛ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ሰልጣኞችን አስመረቀ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2017(ኤፍ ኤም ሲ) የጦላይ ከፍተኛ ባለሌላ ማዕረግተኛ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት 10ኛ ዙር ምልምል ወታደሮች እና የ27ኛ የባለሌላ ማዕረግተኛ ሰልጣኞችን አስመረቀ፡፡
የጦላይ ከፍተኛ ባለሌላ ማዕረግተኛ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ዋና አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል ጡምሲዶ ፊታሞ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ተመራቂዎች ለኢትዮጵያ ዘብ ለመቆም በመብቃታችሁ ክብር ሊሰማችሁ ይገባል።
ተመራቂዎቹ ዘመኑን የሚዋጅ ወታደራዊ ጥበብ እና ሳይንስ መቅሰማቸውን ጠቅሰው፤ በሀገሪቱ ላይ የሚቃጣን ማንኛውም ጥቃት ለመመከት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡
ለተመራቂ ወታደሮች መለዮ እና ማዕረግ የማልበስ ሥነ-ሥርዓትም ተከናውኗል፡፡
በክብሩወሰን ኑሩ