አቢሲንያ ባንክ ከ349 ነጥብ 9 ሚሊየን ዶላር በላይ ብድር አቀረበ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አቢሲንያ ባንክ የውጭ ምንዛሪ እጥረትን ለመፍታትና የገቢ ንግድን ለመደገፍ በበጀት ዓመቱ 349 ሚሊየን 943 ሺህ 588 የአሜሪካ ዶላር ብድር ማቅረቡን አስታወቀ፡፡
ባንኩ ለደንበኞች ካቀረበው የምንዛሪ ድልድል ውስጥ በ3ኛው ሩብ ዓመት ከ1 ሺህ በላይ ደንበኞች ወደ ሀገር ውስጥ የገበያ ዕቃዎችን እንዲያስገቡ 189 ሚሊየን 82 ሺህ 861 ዶላር እንዲያገኙ ማድረጉንም ገልጿል፡፡
ይህም የደንበኞችን ፍላጎት ለማሟላት እያደረገ ያለውን ከፍተኛ ጥረት እንደሚያሳይ ነው የገለጸው፡፡
በቀጣይም የውጭ ምንዛሪ ሀብትን በአግባቡ በማሥተዳደር እና ከሀገራዊ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ጋር በማጣጣም የደንበኞቹን ፍላጎት ለሟሟላት እንደሚሠራ አረጋግጧል፡፡
በውጭ ምንዛሪ ድልድል ረገድ በኃላፊነት በመሥራት ለተረጋጋ ሀገራዊ የኢኮኖሚ ዕድገት እያበረከተ ያለውን አስተዋፅዖም አጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቁሟል፡፡