የጎንደርን የንግድና ኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ለማጠናከር እየተሠራ ነው
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የጎንደር ከተማን የንግና ኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ለማጠናከር የሰላም ሥራዎች ላይ በትኩረት እየተሠራ ነው ሲሉ የከተማዋ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ቻላቸው ዳኛው ገለጹ፡፡
የከተማዋን የንግድና ኢንቨስትመንት ሥራዎች ለማሳደግ ያለመ ውይይት፤ በተለያዩ ዘርፎች ተደራጅተው ከሚሠሩ ወጣቶች ጋር ተካሂዷል፡፡
ሕገ-ወጥ የንግድ እንቅስቃሴን መልክ ለማስያዝ እና የንግድ ሥራውን በዘላቂነት ለማስቀጠል ከባለድርሻ አካላት ጋር እየተሠራ መሆኑን የከተማ አሥተዳደሩ ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ኃላፊ ቴዎድሮስ ፀጋዬ ገልጸዋል፡፡
የአሥተዳደሩ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ቻላቸው ዳኛው በበኩላቸው፤ የንግድ እንቅስቃሴ መቀዛቀዝ ችግሮችን ለማረምና የኢንቨስትመንት ዘርፉን ለማነቃቃት ለሰላም ሥራዎች ትኩረት መሰጠቱን አስረድተዋል፡፡
በቀጣይም የተረጋጋ የንግድ ሥርዓትን በመፍጠር የሕዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንደሚሠሩ ተናግረዋል፡፡
በምናለ አየነው