Fana: At a Speed of Life!

የሊጉ መሪ ሊቨርፑል በፉልሀም ተሸነፈ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ31ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ፉልሀም በሜዳው ክራቨን ኮቴጅ የሊጉ መሪ ሊቨርፑልን አስተናግዶ 3 ለ 2 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

የፉልሀምን የማሸነፊያ ግቦች ሴሴኞን፣ ኢዎቢ እና ሙኒዝ ሲያስቆጥሩ የሊቨርፑልን ግቦች ማክአሊስተር እና ዲያዝ ከመረብ አሳርፈዋል፡፡

ፉልሀም ማሸነፉን ተከትሎ በ48 ነጥብ 8ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ፤ የሊጉ መሪ ሊቨርፑል ከተከታዩ አርሰናል ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ 14 ከፍ የሚያደርግበትን ዕድል ሳይጠቀም ቀርቷል፡፡

በሌላ የሊጉ ጨዋታዎች ቶተንሀም ሆትስፐር በሜዳው ሳውዝሀምፕተንን አስተናግዶ 3 ለ 1 በሆነ ውጤት ሲያሸነፍ፤ ብሬንትፎርድ ከቼልሲ ያደረጉት ጨዋታ ያለ ምንም ግብ ተጠናቅቋል፡፡

የዕለቱ ተጠባቂ ጨዋታ ምሽት 12 ሠዓት ከ30 በኦልድትራፎርድ ስታዲየም ማንቼስተር ዩናይትድን ከማንቼስተር ሲቲ ያገናኛል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.