ሳውዝሃምፕተን ከፕሪሚየር ሊጉ መውረዱ ተረጋገጠ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ31ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሳውዝሃምፕተን ከሜዳው ውጪ ከቶተንሀም ሆትስፐር ጋር ያደረገውን ጨዋታ መሸነፉን ተከትሎ ወደ ሻምፒዮን ሺፕ መውረዱ ተረጋግጧል።
ሳውዝሃምፕተን እስከ አሁን በሊጉ ካደረጋቸው ጨዋታዎች፤ በሁለቱ አሸንፎ በአራቱ አቻ ተለያይቶ በሀያ አምስቱ ደግሞ ሽንፈት አስተናግዷል፡፡
በዚህም በ10 ነጥብ የመጨረሻ የሊጉ የደረጃ ሠንጠረዥ 20ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ሳውዝሃምፕተን፤ ከሊጉ መውረዱን ያረጋገጠ የመጀመሪያው ክለብ ሆኗል።
በወንድማገኝ ፀጋዬ