Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፉ ፓርላማ ህብረት ጉባኤ ላይ እየተሳተፈች ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር የተመራው የፓርላማና የፌዴሬሽን ምክር ቤት የልዑካን ቡድን በኡዝቤኪስታን ታሽከንት ከተማ እየተካሄደ ባለው በ150ኛው በዓለም አቀፉ ፓርላማ ህብረት (አይፒዩ) እየተሳተፈ ይገኛል።

በመድረኩ ኢትዮጵያን በመወከል ንግግር ያደረጉት አፈጉባዔ አቶ አገኘሁ ተሻገር፤ ኢትዮጵያ በህብረቱ ላይ ያላትን አጋርነት አጠናክራ ለመቀጠል ቁርጠኛመሆኗን ገልጸዋል።

ለ2030 የዘላቂ ልማት ግቦች ስኬት የሚመለከታቸው አካለት ዓለም አቀፍ ትብብሮችን እንዲያጠናክሩም ጥሪ አቅርበዋል።

ኢትዮጵያ ሰላምና ብልጽግናን በሀገር አቀፍ ደረጃ ብቻ ሳይሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ እውን ለማድረግ ከ2030 የዘላቂ ልማት ግቦች እና ከአፍሪካ አጀንዳ 2063 ጋር የተጣጣመ አገራዊ የልማት ዕቅድ አውጥታ እየሰራች ትገኛለች ብለዋል።

ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት የዓለም አቀፍ የልማት ግቦችን በማሳካት ረገድ ከፍተኛ እድገት እያሳየች እና ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት እያስመዘገበች መሆኗን ጠቅሰው፤ በተለያዩ ዘርፎች ጉልህ እድገት ማስመዝገቧን ገልጸዋል።

እንዲሁም የአየር ንብረት ለውጥ ተፅእኖን ለመቋቋምና እና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ከ40 ቢሊየን በላይ ችግኞችን በመትከል የአረንጓዴ አሻራ ፕሮግራም እንዲሳካ መስራቷን መናገራቸውን የምክር ቤቱ መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.