Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ለደቡብ ሱዳን ሕዝቦች የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል አረጋገጠች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ ለደቡብ ሱዳን ሕዝቦች የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስታወቁ፡፡

የደቡብ ሱዳን ምክትል ፕሬዚዳንት ቤንጃሚን ቦል ሜል ከሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት ይዘውት የመጡትን መልዕክት መቀበላቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ገልፀዋል፡፡

በዚሁ ወቅትም ከምክትል ፕሬዚዳንቱ ጋር ውጤታማ ውይይት ማድረጋቸውን ነው የገለጹት፡፡

በደቡብ ሱዳን ያለውን ወቅታዊ የጸጥታና የፖለቲካ ችግር ለመፍታትም ሁሉን አቀፍ ቀጣናዊ አካሄድ እንደሚያስፈልግ በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያም ለደቡብ ሱዳን ሕዝቦች ያላትን የድጋፍ ቁርጠኝነት አጠናክራ እንደምትቀጥል አረጋግጠዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.