Fana: At a Speed of Life!

የናይጄሪያ መከላከያ ኃይል ከፍተኛ አመራሮች የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደርን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሜጀር ጄኔራል ዳሂሩ ሳኑሲ የተመራ የናይጄሪያ መከላከያ ኃይል ሪሶርስ ማዕከል ከፍተኛ ልዑክ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደርን ጎብኝቷል።

የአስተዳደሩ ም/ዋና ዳይሬክተር አስቴር ዳዊት፥ የኢትዮጵያን የሳይበር ደህንነት በማረጋገጥ በኩል ተቋሙ በቴክኖሎጂ፣ በሰው ኃይል እና በአሰራር ስርዓት እየሰራቸው የሚገኙ ሥራዎችን በተመለከተ ገለጻ አድርገዋል፡፡

ልዑካኑ በጉብኝታቸው ወቅት ኢትዮጵያ የሳይበር ደህንነት እና ሉዓላዊነቷን ለማስጠበቅ የሚያስችል ብቁና ዘመናዊ ተቋም መገንባት መቻሏን ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ እና ናይጄሪያ በዲፕሎማሲው መስክ ጥብቅ ወዳጅነት ያላቸው ሀገራት መሆናቸውን እና በሳይበር ደህንነት መስክም በጋራ ለመስራት የሚችሉባቸው በርካታ መስኮች መኖራቸውን አመልክተዋል።

የአፍሪካ ሀገራት የሳይበር ደህንነት ተቋማት ስትራቴጂካዊ ትብብርና ቅንጅት በመፍጠር ለአህጉራዊ የሳይበር ደህንነትና ሉዓላዊነት መረጋገጥ መስራት እንደሚገባ መናገራቸውን የአስተዳደሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.