Fana: At a Speed of Life!

በብሪታኒያ በማህበራዊ ትስስር ገጾች የሚፈጸሙ ወንጀሎች መስፋፋት…

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በብሪታኒያ በማህበራዊ ትስስር ገጾች በሚሰራጩ ተገቢ ባልሆኑ መረጃዎች ምክንያት በየዓመቱ ከ12 ሺህ በላይ ግለሰቦች በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንደሚውሉ ተሰምቷል፡፡

ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር የሚውሉት በማህበራዊ ትስስር ገጾች በሚያሰራጯቸው የሰውን ክብር የሚነኩ ስድብ አዘል እና ሌሎች ተገቢ ያልሆኑ ልጥፎች መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ግለሰቦች የጥላቻ እና ሀሰተኛ መልዕክቶችን በማህበራዊ ትስስር ገጾች ያጋሩ፣ የለጠፉ እንዲሁም በቀጥታ ወደ ሌሎች ሰዎች የላኩ መሆናቸው ተጠቅሷል፡፡

በቁጥጥር ስር የዋሉት 12 ሺህ የብሪታኒያ ዜጎች በሀገሪቱ የኮሙኒኬሽን ሕግ 2003/127ን እንዲሁም በ199/1 የተቀመጠውን የጥላቻ ንግግር አዋጅ የጣሱ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

በዚህም በሕፃናት እና ታዳጊዎች እንዲሁም በሌሎች ሰዎች ላይ ጭንቀት እና ሌሎች ሥነ ልቦናዊ ጫናዎች እንዲፈጠሩ አድርገዋል ነው የተባለው፡፡

በብሪታኒያ በፈረንጆቹ 2023 ብቻ 12 ሺህ 183 ግለሰቦች በማህበራዊ ትስስር ገጾች ከሚሰራጩ የተዛቡ፣ ሀሰተኛ እንዲሁም የጥላቻ መረጃዎች ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተሰምቷል፡፡

በብሪታኒያ በግለሰቦች የሚደረጉ እና ተገቢነት የሌላቸው የማህበራዊ ሚዲያ ልጥፎች አሁንም በከፍተኛ ደረጃ እየጨመሩ እንደሚገኙ የተጠቆመ ሲሆን፤በቁጥጥር ስር የሚውሉ ዜጎች ቁጥራዊ አሃዝ በየዓመቱ ከ58 በመቶ በላይ ጭማሪ ሊያሳይ ይችላል ተብሏል፡፡

ከእንግሊዝ በተጨማሪ፣ ባሕሬን፣ ቱርክ፣ ፈረንሳይ፣ አሜሪካ፣ ሳዑዲ ዓረቢያ፣ ሕንድ፣ አውስትራሊ እና ቻይና ከማህበራዊ ትስስር ገጾች ጋር በተያያዘ በርካታ ዜጎቻቸውን በቁጥጥር ስር ያዋሉ ሀገራት መሆናቸውን ታይም መጽሄትን ጠቅሶ አር ቲ ዘግቧል፡፡

በሚኪያስ አየለ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.