በሰሜን ተራሮች የዋልያዎችን ቁጥር ለማሳደግ ያለመ ዕቅድ ይፋ ሆነ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በቀጣዮቹ አምሥት ዓመታት በሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የሚገኙ ዋልያዎችን (አይቤክስ) ቁጥር ወደ 600 ለማሳደግ የሚያስችል ስትራቴጅክ ዕቅድ ይፋ ሆነ፡፡
በስትራቴጂክ ዕቅዱ ላይ በጎንደር ከተማ በተካሄደ ውይይት ላይ የኢትዮጵያ ደንና ዱር እንሰሳት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኩመራ ዋቅጅራ እንዳሉት፤ በሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ዙሪያ በሚከናወኑ ሕገ-ወጥ ተግባራት ምክንያት የዋልያ (አይቤክስ) ቁጥር ወደ 306 ዝቅ ብሏል፡፡
ይህን ተከትሎም የዋልያ አይቤክስን ቁጥር ለመጨመር የሚያስችል ስትራቴጅክ ዕቅድ መዘጋጀቱን አረጋግጠዋል፡፡
የቱሪዝም ሚኒስትር ዴዔታ ስለሽ ግርማ በበኩላቸው መንግሥት ቱሪዝምን እንደ ዋነኛ የኢኮኖሚ ዘርፍ በማየት እየሠራ መሆኑን ገልጸው፤ የዋልያ (አይቤክስ) ቁጥር ከፍ እንዲል ትኩረት መሠጠቱ የሚበረታታ ነው ብለዋል፡፡
በበላይነህ ዘላለም