Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፉ ሀገር በቀል ምርት ፎረም ላይ እየተሳተፈች ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ እና ሌሎች አመራሮች በ3ኛው ዓለም አቀፉ ሀገር በቀል ምርት ፎረም ላይ እየተሳተፉ ነው፡፡

ከዛሬ ጀምሮ ለቀጣይ ሶስት ቀናት የሚካሄደው ፎረሙ በዓለም የጤና ድርጅት አስተባባሪነት በተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች  አቡ ዳቢ ከተማ ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡

ዶ/ር መቅደስ ዳባ በፎረሙ ባደረጉት ንግግር÷ ኢትዮጵያ ከሀገር ውስጥ የመድሐኒት እና የሕክምና መገልገያ ግብዓቶች ምርት ጋር በተያያዘ ያከናወነቻቸውን ተግባራት አስረድተዋል፡፡

በተጨማሪም በቀጣይ በዘርፉ በሀገር፣ በአህጉር እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ትኩረት ሊሰጣቸው በሚገቡ ጉዳዮች ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በፎረሙ የዓለም የጤና ድርጅትና የተለያዩ ሀገራት ተወካዮች የጤና አጠባበቅ ሥርዓቶችን እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ጥንካሬን ለማሻሻል ዘላቂ የሀገር ውስጥና ክልላዊ ምርቶችን ለማሳደግ ወሳኝ በሆኑ ስትራቴጅካዊ ርምጃዎች ዙሪያ እየመከሩ መሆኑን በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.