Fana: At a Speed of Life!

ፋሲል ከነማ ቅዱስ ጊዮርጊስን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ24ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ፋሲል ከነማ ቅዱስ ጊዮርጊስን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

የፋሲል ከነማን የማሸነፊያ ሁለት ግቦች ጌታነህ ከበደ ሲያስቆጥር፤ የቅዱስ ጊዮርጊስን ብቸኛ ግብ አብርሃም ጌታቸው ከመረብ አሳርፏል፡፡

ፋሲል ከነማ ተከታታይ ሦስተኛ ድሉን በሊጉ ሲያሳካ፤ ቅዱስ ጊዮርጊስ ባለፉት ሥድስት የሊጉ ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻለም፡፡

ውጤቱን ተከትሎ ፋሲል ከነማ በ33 ነጥብ 5ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ፤ ቅዱስ ጊዮርጊስ በ31 ነጥብ 9ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡

የሊጉ ጨዋታ ምሽት 12 ሠዓት ሲቀጥል ኢትዮጵያ መድን ከወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.