Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) አቶ ጌታቸው ረዳ ላበረከቱት አስተዋጽኦ አመሰገኑ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አቶ ጌታቸው ረዳ ላለፉት ሁለት ዓመታት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር በመሆን ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትግርኛ ቋንቋ ባስተላለፉት መልዕክት÷“በኢፌዲሪ ሕገ መንግስት 62 (9)፣ አዋጅ 359/1995 አንቀጽ 15(3) እና ደንብ ቁጥር 533/2015 እንዲሁም በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት መሰረት አቶ ጌታቸው ረዳ ላለፉት ሁለት ዓመታት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር በመሆን ላበረከቱት አስተዋጽኦ አመስግነዋል፡፡

በተለይም አቶ ጌታቸው የተገኘው ሰላም እንዲጸና ለነበራቸው ከፍተኛ ጥንቃቄና አመራር የፌደራል መንግስት እውቅና እንደሚሰጥ አስገንዝበዋል፡፡

በቀጣይ ሥራዎች በጋራ ተቀራርበው እንደሚሰሩ ያረጋገጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ÷ ለነበራቸው ቆይታም ምስጋና አቅርበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.