Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሻርጃ ከተማ አዲስ በረራ ሊጀምር ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች ሻርጃ ከተማ ከግንቦት 24 ቀን 2017 ጀምሮ የመንገደኞች የበረራ አገልግሎት ለመጀመር ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታወቀ፡፡

በሣምንት አራት ጊዜ የሚደረገው ይህ የበረራ አገልግሎት፤ መንገደኞች ወደ ሻርጃ ከተማ በተቀላጠፈ አማራጭ በቀላሉ እንዲጓዙ የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በመካከለኛው ምሥራቅ ከ17 በላይ መዳረሻዎች እንዳሉት እና ከ100 በላይ ሳምንታዊ የመንገደኞችና የካርጎ አገልግሎት በረራዎችን እያደረገ መሆኑን በማኅበራዊ ትሥሥር ገጹ አስታውቋል፡፡

ወደ ሻርጃ ከተማ የሚጀምረው የበረራ አገልግሎትም በኢትዮጵያና በተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች መካከል ያለውን የንግድ፣ ቱሪዝምና የባህል ግንኙነት ለማጠናከር እንደሚያስችልም ተጠቅሷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.