Fana: At a Speed of Life!

የሐይማኖት አባቶች በንግግራቸው ሁሉ ሰላምን መስበክ እንደሚጠበቅባቸው ተመላከተ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሐይማኖት ተቋማት እና አባቶች በፀሎታቸውም ሆነ በንግግራቸው ስለ ሰላም መስበክ ዋነኛ ተግባራቸው ሊሆን እንደሚገባ የኦሮሚያ ክልል የሐይማኖት ተቋማት ጉባዔ አስገነዘበ፡፡

ጉባዔው ያዘጋጀው የሰላም ኮንፈረንስ፤ “ሐይማኖቶች ለሠላም፣ ለመከባበር፣ ለአብሮነት እና አንድነት” በሚል መሪ ሐሳብ በጅማ ከተማ ተካሂዷል፡፡

የኮንፈረንሱ ዓላማ፤ ለዘመናት የተሻገረውን አብሮነት እና ሠላም ማፅናት መሆኑን የጉባዔው ምክትል ሰብሳቢ ሼክ ጋሊ ሙክታር አስታውቀዋል፡፡

ሰላም የሁሉም ሐይማኖት መሠረታዊ አስተምኅሮ መሆኑን ጠቅሰው፤ ፀሎትን በሥርዓቱ ማከናወንን ጨምሮ የተለያዩ ሥራዎችን መሥራት የሚቻለው ሰላም ሲኖር መሆኑን በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡

በመሆኑም የሐይማኖት ተቋማት እና አባቶች በፀሎታቸውም ሆነ በንግግራቸው ስለ ሰላም መስበክ ዋነኛ ተግባራቸው ሊሆን እንደሚገባአስገንዝበዋል፡፡

በሙክታር ጠሃ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.