በአማራ ክልል ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ውይይት እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራ ክልል ወቅታዊ የሰላም፣ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ላይ ያተኮረ ውይይት በባህር ዳር ከተማ እየተካሄደ ነው።
በውይይቱ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደና የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፋንቱ ተስፋዬ፤ በብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ይርጋ ሲሳይና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
በውይይቱ በክልሉ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ላይ በማተኮር ምክክር እንደሚደረግ ተገልጿል።
በተጨማሪም በክልሉ ወቅታዊ የሰላምና መረጋጋት ጉዳዮች ላይ በመምከር አቅጣጫዎች እንደሚቀመጡ ኢዜአ ዘግቧል።