ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሃሙድ አሊ ዩሱፍ ጋር ተወያይተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መረጃ÷ ዛሬ ጠዋት ከአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሃሙድ አሊ ዩሱፍ ጋር ተገናኝተን በቁልፍ ቀጠናዊ የሰላም እና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገናል ብለዋል።