Fana: At a Speed of Life!

ተጠባቂው የአርሰናል እና ሪያል ማድሪድ ፍልሚያ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የሩብ ፍፃሜ የመጀሪያ ዙር ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት መደረግ ሲጀምሩ አርሰናል በኤምሬትስ ስታዲየም ምሽት 4 ሠዓት ላይ ሪያል ማድሪድን ያስተናግዳል፡፡

በጥሎ ማለፉ ጨዋታ አርሰናል ፒኤስቪን፤ ሪያል ማድሪድ ደግሞ አትሌቲኮ ማድሪድን አሸንፈው ለሩብ ፍፃሜ መድረሳቸው ይታወቃል።

በየሊጋቸው ሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙት ሁለቱ ቡድኖች በሳምንቱ መጨረሻ ባደረጉት የሊግ ጨዋታ ማሸነፍ አልቻሉም።

አርሰናል እና ሪያል ማድሪድ በፈረንጆቹ 2006 የውድድር ዓመት በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ጥሎ ማለፍ ጨዋታ በተገናኙበት ወቅት አርሰናል በቴሪ ኦንሪ ብቸኛ ግብ ማሸነፉ ይታወሳል፡፡

በተመሳሳይ ምሽት 4 ሠዓት ላይ ባየርንሙኒክ በአልያንዝ አሬና የጣልያኑን ክለብ ኢንተርሚላንን ያስተናግዳል።

ሁለቱ ቡድኖች በሚወዳደሩት ሊግ የደረጃ ሠንጠረዥ አንደኛ ላይ የተቀመጡ ሲሆን፤ በሻምፒየንስ ሊግ ፉክክሩ ለመቆየት ይፋለማሉ።

ባለሜዳው ሙኒክ ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች፤ በቡንደስ ሊጋው ድል ሲቀናው ተጋጣሚው ኢንተር ሚላን በሁሉም ውድድር ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻለም።

ባየርን ሙኒክ የጀርመኑን ክለብ ባየርሊቨርኩሰንን እንዲሁም ኢንተርሚላን ፌይኖርድን በጥሎ ማለፍ ጨዋታው በመርታት ለሩብ ፍፃሜ መድረስ ችለዋል፡፡

በወንድማገኝ ፀጋዬ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.