Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ዕሴቶች እና ኪናዊ ፀጋዎች ለብሪክስ አባል ሀገራት ሊተዋወቁ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ የባህል ዕሴቿን እና ኪናዊ ፀጋዎቿን “የኢትዮጵያ የባህል ድልድይ ሕዝብ ለሕዝብ ትሥሥር” በሚል መሪ ሐሳብ ለብሪክስ አባል ሀገራት ልታስተዋውቅ መሆኗ ተገለጸ።

ሀገር ውስጥ ያሉ ቱባ ባህላዊ ዕሴቶችን፣ ኪናዊ ፀጋዎችን እና የፈጠራ ምርቶችን በመጠቀም ከኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች በተውጣጡ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች ለብሪክስ አባል ሀገራት ለማቅረብ ዝግጅት መጀመሩ ተገልጿል፡፡

ኢትዮጵያ ከብሪክስ አባል ሀገራት ጋር በዲፕሎማሲው መስክ ከምትሠራቸው ሥራዎች አንዱ የባህልና የኪነ-ጥበብ ዲፕሎማሲ መሆኑን የገለጸው ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር፤ በዚህ ልክ አቅዶ እየሠራ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡

ይህንን ዝግጅት ለማቅረብ የሚያስችለውን ስምምነትም ከሻኩራ ፕሮዳክሽን ጋር መፈራረሙን ሚኒስቴሩ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጹ ገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.