Fana: At a Speed of Life!

ከ7 ሺህ በላይ ተሽከርካሪዎች ላይ ድንገተኛ ፍተሻ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴርና ባለድርሻ አካላት ቅንጅት በተካሄደ የተሽከርካሪ የመንገድ ላይ ክትትል እና ድጋፍ 7 ሺህ 51 ተሽከርካሪዎች ላይ ድንገተኛ ፍተሻ ተደረገ፡፡

በአዲስ አበባ እና ሸገር ከተማ አሥተዳደሮች የተካሄደው የተሽከርካሪ የመንገድ ላይ ክትትል እና ድጋፍ አፈጻጸም ተገምግሟል።

በግምገማው ላይ እንደተገለጸው፤ ከ7 ሺህ 51 ተሽከርካሪዎች በተጨማሪ 22 የተሽከርካሪ ቴክኒክ ምርመራ ተቋማት፣ 31 የከተማ ትራንስፖርት ተርሚናሎች እና ዘጠኝ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት መስጫ ላይ ድንገተኛ ፍተሻ ተደርጓል፡፡

በድንገተኛ ፍተሻውም በአሽከርካሪዎች እና ተሽከርካሪዎች ላይ ጉድለቶች መገኘታቸውን የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴዔታ በርኦ ሀሰን በመድረኩ ላይ ገልጸዋል፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር በታዩ ክፍተቶች ላይ ለተቋማት ግብዓት ተሰጥቷል፤ ማስተካከያዎችም እየተወሰዱ ነው ማለታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡

በድንገተኛ ፍተሻው የታዩ ግሮችን ለመቅረፍም የተሽከርካሪ መርማሪ ተቋማት እና የአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማት ላይ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ቁጥጥር እንደሚደረግ አረጋግጠዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.