ኢትዮጵያ ወንጀልን በመከላከል ላይ እየሠራቻቸው ያሉ ተግባራትን ለተለያዩ ሀገራት ተወካዮች አቀረበች
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ፍትሕ ሚኒስቴር ከወንጀል መከላከል ጋር በተያያዘ በኢትዮጵያ እየተሠሩ ያሉ ሥራዎችን ለተለያዩ ሀገራት እና ዓለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች አቀረበ፡፡
የተባበሩት መንግሥታት 15ኛው የወንጀል መከላከልና የወንጀል ፍትሕ ኮንግረስ የአፍሪካ አኅጉር የቅድመ ዝግጅት ስብሰባ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡
በመድረኩ ላይ በፍትሕ ሚኒስቴር የመንግሥት ሕግና ፍትሕ አገልግሎት ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ በላይሁን ይርጋ በኢትዮጵያ ከወንጀል መከላከል ጋር በተያያዘ ፖሊሲና ስትራቴጂ ከመቅረጽ፣ ሕጎችን ከማውጣት እና ከመተግበር ጀምሮ እየተሠሩ ያሉ ሥራዎችን አብራርተዋል፡፡
በቀጣይ ሊሠሩ በታቀዱ ተግባራት ዙሪያም ለተለያዩ ሀገራት እና ዓለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች በማቅረብ የልምድ ልውውጥ መደረጉን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡