Fana: At a Speed of Life!

ኮሚሽኑ በአማራ ክልል ከሚገኙ ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ጋር እየተወያየ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአማራ ክልል ከሚገኙ ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች አካላት ጋር ውይይት እያደረገ ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር መላኩ ወልደማርያም ባደረጉት ንንግር፤ ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦቹ  መሠረታዊ በሆኑ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ እንዲነጋገሩ እና ለሀገር መፍትሔ የሚባሉ አጀንዳዎችን እንዲያመላክቱ ጠይቀዋል፡፡

የሀገረ መንግሥት ህልውናና ቅቡልነትን የሚፈታተኑ፣ በተለመደው ሕግና ፖሊሲ ማዕቀፍ ሊፈቱ ያልቻሉና ሀገራዊ አብሮነትን አዳጋች የሚያደርጉ አጀንዳዎችን በመለየት ረገድ ተሳትፎ እንዲያደርጉም አሳስበዋል፡፡

ምክክር ዋና ዓላማው እውነትን በማፈላለግ በሕዝቦች መካከል አለመተማመን እንዲፈጠር ያደረጉ የተሳሳቱ ትርክቶችን ማምከን ነውያሉት ደግሞ የኮሚሽኑ ሌላኛው ኮሚሽነር ዮናስ አዳዬ (ዶ/ር) ናቸው፡፡

ለዚህ ዓላማ መሳካትም የተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ሚና ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው፤ በሂደቱ የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

በአማራ ክልል የሚገኙ ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች የተረጋጋ ሀገረ መንግሥት በመመሥረት ሂደት የላቀ ሚና እንዳላቸውም ገልጸዋል።

ነገ ስድስተኛ ቀኑን በሚይዘው የአማራ ክልል የምክክር መድረክ፤ የባለድርሻ አካላት ምክክር እንደሚጀመር ተጠቁሟል፡፡

በመሳፍንት እያዩ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.