Fana: At a Speed of Life!

በውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት የተሻለ አፈፃፀም ለማስመዝገብ መትጋት ያስፈልጋል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት የተሻለ አፈፃፀም ለማስመዝገብ የተቀናጀና የተናበበ ሥራ መሥራት እንደሚያስፈልግ የሥራና ክኅሎት ሚኒስትር ዴዔታ ዳንኤል ተሬሳ ገልፀዋል።

ሚኒስቴሩ የአሠሪና ሠራተኛ ዘርፍ የዘጠኝ ወር ዕቅድ አፈፃፀም የተገመገመ ሲሆን፤ በዚሁ ወቅት በአሠሪና ሠራተኛ ግንኙነት ዙሪያ የተያዙ ዕቅዶችን ከማሳካት አንፃር ከፍተኛ መሻሻሎች መኖራቸውን ሚኒስትር ዴዔታው ገልጸዋል፡፡

ዘርፉን በቴክኖሎጂ ማዘመን፣ የወሳኝ ቦርድ አደረጃጀትን በክልሎች ማስፋትና የሙያ ደኅንነትና ጤንነትን ጉዳይ በሁሉም የሥራ ቦታዎች ትኩረት እንዲያገኙ ማድረግ የሚያስችል ንቅናቄ መፍጠር የቀጣይ አቅጣጫዎች መሆናቸውን አብራርተዋል፡፡

በበጀት ዓመቱ የማጠቃለያ ምዕራፍ የክልሎችን ዐቅም የማጠናከር ሥራ በትኩረት እንደሚሰራ መናገራቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.