Fana: At a Speed of Life!

እንዳሻው ጣሳው (ዶ/ር) የዜጎችን ኑሮ በዘላቂነት የሚቀይሩ ሥራዎች እየተሠሩ መሆኑን ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለመሸጋገር የማሕበረሰብ ጥሪት ግንባታና የቤተሰብ ኑሮ ማሻሻያ ሥራዎች አፈፃፀም በሆሳዕና ከተማ ተገምግሟል፡፡

ርዕሰ መሥተዳድሩ በግምገማው ላይ እንዳሉት፤ በክልሉ የዜጎችን ኑሮ በዘላቂነት መቀየር በሚያስችሉ ተግባራት ላይ በትኩረት እየተሠራ ነው።

ዜጎች በቋሚነት ራሳቸውን የሚችሉበትን ስልት በመቀየስ መሥራት እንደሚገባ ገልጸው፤ የፕሮጀክቱን አፈፃፀም በኦዲት ማረጋገጥ እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል፡፡

በተጨማሪም ሕዝቡን በማስተባበር በራስ ዐቅም የሰብዓዊ ድጋፍን አስተማማኝ ለማድረግ፤ የተጀመረውን የምግብ ክምችት ማጠናከር እንደሚገባ አስረድተዋል፡፡

ሌብነት እና ብልሹ አሠራርን በመከላከል የተገኘውን ሀብት ለታለመለት ዓላማ ለማዋልም ዘርፉን በጥብቅ ዲሲፕሊን መምራት ይገባል ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.