የአማራ ክልል ቀጣዩን የሀይማኖት ኮንፈረንስ የሚያዘጋጅ ክልል ሆኖ ተመረጠ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ)የአማራ ክልል ቀጣዩን የሀይማኖት ኮንፈረንስ የሚያዘጋጅ ክልል ሆኖ በመመረጥ የአዘጋጅነት ዋንጫውን ተረክቧል፡፡
በኦሮሚያ ክልል የሀይማኖት ተቋማት ተዘጋጅቶ “የሀይማኖት ተቋማት ለሁለንተናዊ ሰላምና እርቅ”በሚል መሪ ቃል በጅማ ከተማ ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየ ሲሆን በዚህም ከመላ ሀገሪቱ የሀይማኖት ተቋማት መሪዎችና የሚመለከታቸው አካላት ተገኝቷል።
ከድሬዳዋ የአዘጋጅነትን ሚና የተቀበለው የኦሮሚያ ክልል ለቀጣዩ አዘጋጅ አማራ ክልል ዋንጫውን አስረክቧል።
የአዘጋጅነት ዋንጫውን የአማራ ክልል ተወካዮች ከሰላም ሚኒስቴር ዲኤታው ኸይረዲን ተዘራ(ዶ/ር) ተረክበዋል።
አብዱረህማን መሀመድ