Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮ ኤሌክትሪክና ሀዋሳ ከተማ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ24ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ሀዋሳ ከተማ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል፡፡

የኢትዮ ኤሌክትሪክን ግብ አቤል ሃብታሙ ሲያስቆጥር÷ አሊ ሱሌማን ደግሞ የሀዋሳ ከተማን የአቻነት ግብ በፍጹም ቅጣት ምት ከመረብ አሳርፏል፡፡

ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮ ኤሌክትሪክ በ29 ነጥብ 11ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ÷ ሀዋሳ ከተማ በ21 ነጥብ 15ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡

እንዲሁም 12 ሠዓት ላይ በተደረገ ጨዋታ ሲዳማ ቡና ስሑል ሽረን በፍቅረየሱስ ተ/ብርሃን ብቸኛ ግብ አሸንፏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.