የናይጄሪያ ወታደራዊ ልዑክ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎበኘ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በናይጄሪያ የመከላከያ መረጃ ዋና ኃላፊ ፓርከር አንዳያዳይ የተመራ ወታደራዊ ልዑክ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎብኝቷል።
በጉብኝ ወቅትም የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ታዬ ግርማ (ዶ/ር) ለልዑካን ቡድኑ አባላት ገለፃ አድርገዋል።
በገለፃቸውም፤ ኢንስቲትዩቱ “አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ለሁሉም” በሚል መሪ ሐሳብ ከሚሠራቸው ሥራዎች በተጨማሪ የአፍሪካ ሀገራት የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ተቋም እንዲያቋቁሙ መነሻ መሆን መቻሉን ተናግረዋል፡፡
አፍሪካ ውስጥ በዘርፉ በቂ የሰለጠነ የሰው ኃይል አለመኖር አኅጉሪቱ በሚፈለገው ደረጃ ተጠቃሚ እንዳትሆን እንቅፋት ሆኗል ማለታቸውን የኢንስቲትዩቱ መረጃ አመላክቷል፡፡
ጎብኝዎቹ በበኩላቸው፤ ኢንስቲትዩቱ ከአኅጉር አልፎ በዓዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ለመሆን የሚያስችል ግዙፍ ዳታ ሴንተር መገንባቱን አድንቀዋል።
የሰው ሃብት ልማት ላይ እየሠራ ያለው ሥራም የሚያኮራ መሆኑን ገልጸው፤ ይህም ለአፍሪካ ሀገራት አርዓያ ያደርገዋል ብለዋል፡፡