Fana: At a Speed of Life!

አብዲከሪም ሼኽ ሙሴ (ቀልቢ ደጋህ) የኦብነግ ተጠባባቂ ሊቀመንበር ሆኑ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኦብነግ ማዕከላዊ ኮሚቴ አብዲከሪም ሼኽ ሙሴን (ቀልቢ ደጋህ) የግንባሩ ተጠባባቂ ሊቀመንበር አድርጎ ሰየመ፡፡

የኦጋዴን ነፃ አውጪ ግንባር (ኦብነግ) እያካሄደው ባለው 2ኛ መደበኛ ስብሰባ ከኃላፊነታቸው በተነሱት አብዲራህማን ማሃዲ ምትክ የግንባሩ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀ መንበር የነበሩትን አብዲከሪም ሼኽ ሙሴን የግንባሩ ተጠባባቂ ሊቀመንበር አድርጎ መሰየሙን አስታውቋል፡፡

የግንባሩን ሊቀመንበር በጠቅላላ ጉባዔ እስከሚመረጥ ድረስ አብዲከሪም ሼኽ ሙሴ የግንባሩ ተጠባባቂ ሊቀመንበር ሆነው እንዲቀጥሉ ኮሚቴው ወስኗል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.